ልጅዎት ሂሳብ ይቸግረዋል/ታል ?🤔
ልጅዎት በሂሳብ ትምህርት ለምን እንደሚቸገር/እንደምትቸገር ማወቅ እና ለዚህም እክል መፍትሔ ማግኘት ይፈልጋሉ ? ከዚህ በታች ያለውን እንዲያነቡና ልጅዎ የትኛው እክል እንደገጠማቸው እንዲለዩ እንጋብዛዎታለን
1⃣ ''ሂሳብ ከባድ ነው'' የሚል ልማዳዊ አስተሳሰብ (Math Anxiety and Myth) 🙀
ከታላላቆች ወይንም ከወላጆች የሚሰማ ''ሂሳብ ከባድ ነው'' የሚል ተደጋጋሚ ንግግር ምክንያት ልጆች ሒሳብን ሊጠሉት እና ለመለማመድ ፍላጎት ያጣሉ፡፡ ይህም ምክንያት በዚህ ትምህርት ደካማ እንዲሆኑ ያደርጋል ከዚህ ባለፈ እንዲፈሩትና በጣም ከባድ ነገር እንደሆነ በማሰብ ከመለማመድ እና ጊዜ ሰጥቶ ከመስራት ይታቀባሉ፡፡
2⃣ መሰረት አለመያዝ (Lack of foundational skills) ⛔️
ከታች ክፍል ጀምሮ ያለውን መሰረታዊ የሂሳብ እውቀት አለመያዝ ከፍ ባሉ ተማሪዎች ሳይቀር በብዛት የሚታይ ክፍተት በመሆኑ በደረጃቸው ያለውን የሂሳብ ትምህርት ለመረዳት እና ለመስራት እጅግ በጣም ይቸገራሉ፡፡ ስለዚህ ልጆች ከታች ጀምሮ መሰረት እየያዙ እንዲማሩ ማድረግና ለቀጣይ የክፍል ደረጃቸው የሚመጥን እውቀት እንዲኖራቸው ማስተማርና ክትትል ያስፈልጋል፡፡
3⃣ ትኩረት ለማድረግ መቸገር (Lack of Attention) 🔴
በተለይም ከፍ ባሉ የክፍል ደረጃዎች ያለው ሂሳብ የአንድን ጥያቄ መልስ ለማግኘት የተለያየ አካሄዶችን መሄድ ስለሚያሰፈልግ በጥሩ መልኩ ለመስራትና መልሱን ለማግኘት ያልተበታተነ ትኩረት ለሂሳብ ትምህርት እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ ከታች ባሉ የክፍል ደረጃዎችም ስንመጣ ማናኛውንም የሂሳብ ጥያቄ ለመስራትና ትምህርቱን ለመረዳት ልጆቻችን የሚሰሩት ነገር ላይ ትኩረት አድርገው መስራታቸው ምንም አማራጭ የሌለው ነገር ነው፡፡
ስለዚህ ልጆዎት ትኩረት ማድረግ ባቃታቸውና የሂሳብ ክህሎታቸው ሲቀንስ በተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ሲሳሳቱ ወይንም በፈተና ጥሩ ውጤት ሳያመጡ ሲቀሩ ራስን መውቀስ እና በራስ መተማመናቸው እየቀነሰ ይመጣል ይህም ከክፍል ጓደኞቻቸው እያነሱ እንደሆነና ለራሳቸው ዝቅተኛ ግምት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡
4⃣ በቂ ልምምድ አለማድረግ (Lack of practice) 🥺
ልጅዎት በሂሳብ እየተቸገረ ነው ? ምክንቱም በቂ ጊዜ ሰጥቶ/ታ እየተለማመደ/ች አይደለም በተጨማሪም ሽምደዳ ላይ አተኩሯል ፡፡
ጎበዝ እንኳን ቢሆን ክፍል ውስጥ ቢረዳም በራሱ የመለማመድ እና የመስራት ጊዜ ከሌለው/ላት ረፍዶም ቢሆን ሂሳብ ላይ መቸገሩ አይቀርም፡፡
ለማንኛውም ተማሪ በክፍል ውስጥ የተማረውን እና መልመጃዎችን ጊዜ ሰጥቶ መለማመድ በሂሳብ ትምህርት ስኬታማ ለመሆንና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ይረዳናል፡፡
5⃣ ትዕግስት ማጣት (Lack of patience) 🙃
ምክንያቱም ሂሳብ እንድን ጥያቄ ለመስራት ረዘም ያለ ሂደቶችን መሄድ ይኖርብናል ስለዚህ ሌላው ትምህርት ላይ ካለው በተለየ መልኩ የያዛነውን እስክንጨርስ በትዕግስት መስራት ይኖርብናል፡፡
አንዳንድ ተማሪዎች አንድን ጥያቄ ረዘም ላለ ሰዓት የመስራት ትዕግስት ላይኖራቸው ይችላሉ እነዚህን ተማሪዎች አዝናኝ እና በጨዋታ መልክ ሂሳብን ማስተማር ያስፈልጋል፡፡ ቢሆንም ልጆች በልጅነታቸው ትዕግስት እንዲኖራቸው አድርጎ ማሳደግና እንዲያጎለብቱት መርዳት ያስፈልጋል፡፡
6⃣ አካባቢያዊ ተጽዕኖ (Environmental factors) ⛰️🏔️
ከላይ ከጠቀስናቸው በተለየ መልኩ ተማሪዎችን አካባቢያዊ ተጽዕኖ ሂሳብ ላይ ያላቸውን ችሎታ እና የመስራት አቅም ሊያዳክም ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ከወላጆች በቂ ድጋፍና ማበረታቻ አለማግኘት፣በቂ መጽሐፍትን አለማግኘት ፣ ጥሩ ትምህርት ቤት አለመማር እና የመሳሰሉት ተማሪዎች በሂሳብ ትምህርት ደካማ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡
7⃣ የመማር እክል (Learning disabilities) 📚
የልጆችን ሂሳብ የመረዳት አቅም የሚቀንሱ የተለያዩ የመማር እክሎች አሉ፡፡